የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ተሽከርካሪዎች የመድን ዋስትና የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጀቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Amhara Rural Roads Construction Agency (የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ገመኮኤ 05/2017
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ተሽከርካሪዎች የመድን ዋስትና የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጀቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- የሚገባዉ ተሸከርካሪዎች የመድን ዋስትና የአገልግሎት ግዥ ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በኤጀንሲዉ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ወይም በአማራ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 9900020983896 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል በመያዝ ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ደረሰኝ በማስቆረጥ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ14/08/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 29/08/2017 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013197966 ወይም በአማራ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 9900020983896 ገቢ በማድረግ የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ኦርጅናል ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማስያዝ አለባቸው፣ሆኖም የጠቅላላ ዋጋው 1% ከብር 500,000.00 /ከአምስት መቶ ሺህ ብር/ የሚበልጥ ከሆነ 500.000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ማለትም ዋና እና ኮፒ (Original and Copy) በማለት በተለያየ ፖስታ በአንድ ኤንቨሎፕ በጥንቃቄ በማሸግ በኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 08 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 14/8/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ቀን 29/08/ ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ቫትና ሌሎች ወጭን ጨምሮ መሆን አለበት።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው ዋና መ/ቤት ግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ወይም አዳራሽ በቀን 29/08/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ግዥ ኤጀንሲው አዳራሽ ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
- ኤጀንሲዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር / ቢሮ ቁጥር 08 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፦ 058 222-1115/058-320-7769 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ መሙያ ገፅ ላይ ፊርማና ማህተም ማድረግ አለባቸው። በተጨማሪም በዋጋ መሙያው ላይ ስርስ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገጠር መንገዶች
ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ
