Tender Detail

Tender Details

  • Company ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address 22 ኢየሩስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251118212214
  • Website
  • Deadline13 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-13 00:00:00
  • Categories Vehicle Battery

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/012/2017 የአውቶቡስ መለዋወጫ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ADDIS ABEBA CITY BUS SERVICE ENTERPRICE (የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት)


 

የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በግዥ መለያ ቁጥር አአከአአድ/ብግጨቁ/012/2017 የአውቶቡስ መለዋወጫ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን፡-

1. በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኮፒ (Valid Trade Licensee):

2. በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢዎች ዝርዘር ውስጥ ስለመግባቱ በድረ-ገፅ የተመዘገበበት ኮፒ፣

3. የታክስ ከፋይ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣

4. የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒ (VAT) Certificate)

5. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ ፈቃድ (Valid Tax Clearance Certificate)፣

6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብር 1,600,000.00 (አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ብር) በማቅረብ በግልፅ ጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ አቅራቢዎች (ድርጅቶች) ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ እስከ ምሳ ሰዓት (6፡00 ሰዓት) የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 22 እየሩስ ህንጻ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት (ማዕከል) የግዥ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ በመለየት እስከ ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 7-02 ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር7-02 ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፤

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡ 0118 21 22 14

አዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት

በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡

 

የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender