በአፈ/ ከሣሽ መላ ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኃላ/ተ/የግ/ማህበር እና በአፈ/ተከሣሽ ኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዘር ማኑፋክቸሪንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስለአለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ ለፍርዱ ማስፈጸሚያ የሚሆነውን የአፈ/ተከሳሽ ንብረት የሆኑትን የተለያዩ ብረቶች በጨረታ እንዲሸት ፍርድቤቱ አዟል። ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ ከሣሽ መላ ኢንጅነሪንግ ኮንስትራክሽን ኃላ/ተ/የግ/ማህበር እና በአፈ/ተከሣሽ ኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዘር ማኑፋክቸሪንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስለአለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ፡- ለፍርዱ ማስፈጸሚያ የሚሆነውን የአፈ/ተከሳሽ ንብረት የሆነውን
1ኛ ባለ 8 ብረት ብዛት 2110 ቤርጋ የአንዱ ግምት መነሻ ዋጋ 683.33 (ስድስት መቶ ሰማኒያ ሶስት ብር ከሰላሳ ሶስት ሳንቲም)
2ኛ ባለ 10 ብረት ብዛት 7020 ቤርጋ የአንዱ ብረት የግምት መነሻ ዋጋ 1,076.67 (አንድ ሺ ሰባ ስድስት ብር ከስልሳ ሰባት ሳንቲም)
3ኛ ባለ 12 ብረት 940 ቤርጋ የአንዱ ግምት መነሻ ዋጋ 1,556.67 (አንድ ሺ አምስት መቶ ሃምሳ ስድስት ብር ከስልሳ ሰባት ሳንቲም) ንብረቱ በሚገኝበት በደ/ብርሃን ከተማ ባህር ሀይል ቀበሌ በተከሳሹ ድርጅት ግቢ ውስጥ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
ስለዚህ ፡-
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዚያ 29 ቀን 2017 ዓ/ም ባለ 8 ብረት ቤርጋ ከ ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት ባለ 10 ብረት ቤርጋ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 7፡00 ሰዓት ባለ 12 ብረት ቤርጋ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ይሆናል፡
- ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ እና የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ወዲያውኑ ያሸነፉበትን 1/4ኛውን ለሃራጅ ባዩ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
- ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው የአፈጻጸም ተከሳሽ የተወሰነበትን 9,243,382.62 (ዘጠኝ ሚሊዮን ሁለት መቶ አርባ ሶስት ሺ ሶስት መቶ ሰማኒያ ሁለት ብር ከስልሳ ሁለት ሳንቲም) ለማስከፈል ነው::
- ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሃራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል ፡
- የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል፡፡
የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ደ/ብርሃን
