Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን
  • Address አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-111-0994
  • Websitehttps://www.ethiotelecom.et
  • Deadline07 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-07 00:00:00
  • Categories Building Construction

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በአቦምሳና በደሎመና የሻወርና የመጸዳጃ ቤት ስራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን


 

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በአቦምሳና በደሎመና የሻወርና የመጸዳጃ ቤት ስራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ ሕጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ ሁለት አመት የስራ ልምድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራክተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

መስፈርት፡-

  1. ጨረታው ከሚያዝያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ ፣ የተእታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 20,000.00 (ሀያ ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994 / 022-112-1660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን

 

Save Tender