Tender Detail

Tender Details

  • Company የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አዳማ ከተማ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 022-211-1873
  • Website
  • Deadline06 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-06 00:00:00
  • Categories

በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ፅ/ቤት ዲጂታል የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- አገ 12/2017

 

በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ፅ/ቤት ዲጂታል የስራ ሰዓት መቆጣጠሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

              1. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ እንዲሁም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ያልተከለከሉ መሆን አለባቸው::
              2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዳማ ከተማ የቀድሞው ጅንአድ ፊት ለፊት በሚገኘው የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 403 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
              3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከ4:15 ሰዓት በፊት ለጨረታው የሚያስፈልግ ማንኛውንም የጨረታ ሰነድ በቅ/ጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው:: በመሆኑም የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
              4. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ፣ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4:15 ሰዓት ታሽጎ በ4:30 ሰዓት በቅ/ጽ/ቤቱ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ይከፈታል፡፡
              5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ፅ/ቤት (Ministry Of Revenue Adama Branch Office) ስም አሰርተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
        1. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር፡- +251-2-22-11-40-10 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በገቢዎች ሚኒስቴር የአዳማ ቅ/ፅ/ቤት

 

Save Tender