በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር የ17/18 ህ/ል/ማዕከል የአዳራሽ እድሳት ሥራ እና የአፈር ምርመራ ስራዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማህበር የ17/18 ህ/ል/ማዕከል
በአስቸኳይ በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር የ17/18 ህ/ል/ማዕከል የአዳራሽ እድሳት ሥራ እና የአፈር ምርመራ ስራዎችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ፡-
|
የሥራ አይነት |
|
|
ሎት 1 |
የአዳራሽ እድሳት |
|
ሎት 2 |
የአፈር ምርመራ |
ሲሆን ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ይሆናል፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ከሚመለከተው መስሪያ ቤቶች ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልፅ ክሊራንስ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ መስራታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ከዚህ በፊት ከሁለት ጊዜ በላይ የመልካም ሥራ አፈፃፀም የሥራ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ሠነድ ሊወስዱ ሲመጡ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሠነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለሎት 1 የሥራ አይነት ተወዳዳሪዎች በዘርፍ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ለሎት 2 የሥራ አይነት ተወዳዳሪዎች በዘርፍ ደረጃ 2 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከአንድ በላይ መውሰድ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ሁሉንም የታሸጉ ሰነዶች በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በተጨማሪም ኮንትራክተሮች የጠቅላላ ዋጋ የጨረታውን 2% በCPO (በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በወጣበት በስድስተኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ የጨረታው ሣጥን ይዘጋል እና በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ በ17/18 ህ/ል/ማዕከል በአስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡ ይህ ከሆነ ተጫራቾቹ ያስገባው ሰነድ ውድቅ ይሆናል፡፡ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 (ለአምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን እስከ 6፡00 ሰዓት ጨምሮ የሚቆይ ሲሆን እስከ ስድስተኛ ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ ሰነዳቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታው ሳጥን መከፈቻ ሥነ-ሥርዓትን አያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታ ሳጥን ከታሸገ እና ሠነዶችን መክፈት ከተጀመረ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡ የጨረታውን መመሪያ አለማክበር ከጨረታው ያሰርዛል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ ከቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ወረድ ብሎ በድሪያ ሲት ሞል ፊት ለፊት 17/18 መዝናኛ ማዕከል
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011 662 9510/011 618 6352/011 662 2196 መደወል ይችላሉ።
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የፋና ቦሌ ሸ/ኃ/የተ/የህ/ሥ/ማህበር የ17/18 ህ/ል/ማዕከል
