Tender Detail

Tender Details

  • Company የካ ሳይት 2 የኮንዶሚኒየም ቤት ባለቤቶች ማህበር
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0924448735
  • Website
  • Deadline28 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-28 00:00:00
  • Categories

የካ ሳይት 2 የኮንዶሚኒየም ቤት ባለቤቶች ማህበር በግቢው ለሚገኙ ሕንጻዎች የቀለም ቅብ ሥራና ሻዶው ላይት ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

የካ ሳይት 2 የኮንዶሚኒየም ቤት ባለቤቶች ማህበር


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የካ ሳይት 2 የኮንዶሚኒየም ቤት ባለቤቶች ማህበር በግቢው ለሚገኙ ሕንጻዎች የቀለም ቅብ ሥራና ሻዶው ላይት ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

ስለዚህ፦

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት እና የሥራ ሰዓት በማኅበሩ ጽ/ቤት በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች በሥራው መስክ የተሰማሩ፣ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የሥራ ተቋራጭ መሆናቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፤
  3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው፤
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማኅበሩ ስም አስጽፈው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋውን በሰም በታሸገ ፖስታ አንድ የፋይናንሻል (ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ) ዶክመንቶችን በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ11ኛ ቀን ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን በ8፡00 ሰዓት በማኅበሩ ቅጥር ግቢ በሚገኘው የሕጻናት መዋያ ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት ኣያስተጓጉልም፤
  7. የጨረታው አሸናፊ በጊዜው ቀርቦ ውል የማያስር ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያነት ያስያዘው ሲፒኦ (CPO) አይመለስለትም፤
  8. ማኅበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. ስለጨረታው መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0924448735 ወይም 0116686883 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
  10.  በጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመሳሳይ ሥራ በመሥራት የመልካም አፈጻጸም ምስክርነት ማያያዝ ዋጋ አለው (ተመራጭነት ይኖረዋል)

 

የካ ሳይት 2 የኮንዶሚኒየም ቤት ባለቤቶች ማህበር

 

Save Tender