መሐል ፒያሳ ነጋዴዎች አክሲዮን ማህበር ሊያስገነባ ላሰበው በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 በስሙ የተመዘገበ ይዞታ ላይ ሊያስገነባው ላሰበው B3+G-13 ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ህንፃ ዲዛይን የኮንስትራክሽን አስተዳደርና የግንባታ ቁጥጥር ፍቃድ ያላቸው አማካሪ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
መሐል ፒያሳ ነጋዴዎች አክሲዮን ማህበር
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር MPTS-001
መሐል ፒያሳ ነጋዴዎች አክሲዮን ማህበር ሊያስገነባ ላሰበው በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 በስሙ የተመዘገበ ይዞታ ላይ ሊያስገነባው ላሰበው B3+G-13 ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ህንፃ ዲዛይን የኮንስትራክሽን አስተዳደርና የግንባታ ቁጥጥር ፍቃድ ያላቸው አማካሪ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ ዝቅ ብሎ ከሞናርክሆቴል ጎን ባለው ኑሃ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 04 የማይመለስ 500 ብር በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
1ኛ በፌደራል ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአማካሪ ድርጅት ደረጃ 1 ፍቃድ ያላቸው 2ኛ የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ከግብር ነፃ መሆናቸውን ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ዶክመንቶች ለቴክኒካል 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ፣ ለፋይናሻል 1 ኦርጅናልና 1 ኮፒ በማዘጋጀት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በአካል ቀርበው አክሲዮኑ ማህበሩ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎችቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ተጫርተው ካሸነፉ በኋላ አገልግሎታቸው ጥራት የሌለውና ቀልጣፋ ካልሆነ የውል ጊዜን የምናቋርጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
መሐል ፒያሳ ነጋዴዎች ማኅበር
