Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline14 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-14 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን እና የመንገድ ስራ ተቋራጮችን እና የመንገድ ስራ ተቋራጮችን (GC/RC-1) በጨረታ አወዳድሮ የቀብሪ ዳር የአውሮፕላን መንደርደሪያ መልሶ ግንባታ፣ መዳረሻ መንገድ እና የመኪና ማቆሚያ ቦታ ጥገና ፕሮጀክት ዲዛይን እና ግንባታ (Design-Build of Kebri Dhar Airfield Reconstruction, Access Road and parking area rehabilitation Project) ለማሰራት ይፈልጋል::

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SSNT-T533

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ ደረጃ 1 ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን እና የመንገድ ስራ ተቋራጮችን እና የመንገድ ስራ ተቋራጮችን (GC/RC-1) በጨረታ አወዳድሮ የቀብሪ ዳር የአውሮፕላን መንደርደሪያ መልሶ ግንባታ፣ መዳረሻ መንገድ እና የመኪና ማቆሚያ ቦታ ጥገና ፕሮጀክት ዲዛይን እና ግንባታ (Design-Build of Kebri Dhar Airfield Reconstruction, Access Road and parking area rehabilitation Project) ለማሰራት ይፈልጋል::

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተፈቀደለት አካል በምድብ GC/RC-1 ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPPAA) የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሁለት (2) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶች ላይ የተሰማሩ ተጫራቾች የእያንዳንዱ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ70% በታች ከሆነ በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T533 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 / አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ለ150 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ረቡዕ ግንቦት 6 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 05:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ በ 05:30 ሰዓት ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

ስልክ ቁጥር 011-517-4028

ኢ-ሜይል: AynalemAy@ethiopianairlines.com

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

 

Save Tender