በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የማሪታይምና ሎጀስቲክስ አካዳሚ ለ2017 በጀት ዓመት office equipment በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የማሪታይምና ሎጀስቲክስ አካዳሚ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር-RFQ ESLSE/BABO/
NEG/2024/00142
በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የማሪታይምና ሎጀስቲክስ አካዳሚ ለ2017 በጀት ዓመት office equipment በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Office equipment ግዥ
በዚህም መሰረት፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት የምስክር ወረቀት፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልገሎት ድረ-ገፅ (web site) ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን የሚያሳይ (supplier list) የምስክር ወረቀት፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ ስልጣን ካለው አካል የተሰጠ ማስረጃ (Valid tax clearance)
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሞልቶ የሚመልሰው በድርጅቱ ድረ- ገጽ (WWW.ESLSE. COM) ላይ በERP SYSTEM በዋና መ/ቤት ምዝገባ ካካሄዱ በኋላ ብቻ (ከዚህ ቀደም ያልተመዘገቡ ከሆነ) በሚሰጣቸው መለያ ቁጥር መሰረት የሚሞሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- የጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜ ሲስተሙ ላይ በሚወጣው ቀን እና ሰዓት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስያዣ ሲፒኦ 2% የሚወዳደሩበትን ዋጋ ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ቢሾፍቱ በሚገኘው አካዳሚ የሚገባ ይሆናል፡፡
- አካዳሚው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 011-4-30-51-01/ 09-75-55-73-75 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ የማሪታይምና ሎጀስቲክስ አካዳሚ
