በአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት መደበኛ ካፒታል በጀት G+1 የህንጻ ግንባታ በጉልበት ዋጋ ለማስገንባት ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት
የሀገራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት መደበኛ ካፒታል በጀት G+1 የህንጻ ግንባታ በጉልበት ዋጋ ለማስገንባት ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ተሻሽሎ በወጣው በመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 28/2010 ዓ/ም መሰረት፡-
- ደረጃቸው BC/GC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮች ሆነው የ2017 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የ2017 ዓ/ም የዘመኑ ግብር የከፈሉ ቤት መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት የተመዘገቡበትን ሠርተፊኬት) ማቅረብ የሚችል፤
- ጨረታውን ካሸነፉ በኃላ ከሽያጭ ዋጋ ላይ ለመንግስት ግብር 2% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆኑ ፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ ሆነው ኦርጂናል ዶክመንታቸውን ለማመሳከሪያ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት (የአቅራቢነት መረጃ ኤሌክትሮኒክ ኦን ላይን የተመዘገቡበትን) ማቅረብ የሚችል፤
- ትላልቅ ህንጻ ግንባታ ላይ የሰሩበትን ከመንግስት መ/ቤት የመልካም የስራ አፈጻጸም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በስራና ከተማ ልማት ሚ/ር የተመዘገቡበትና ኦሪጂናል ሕጋዊ የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለ2017 ዓ/ም ያደሱበትን ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የፋይናንሽያል ጨረታ ሰነዱ ዋጋ ተሞልቶ አንድ ኦርጂናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒው በተለያዩ ፖስታ በሰም ታሽጎ ኦርጂናልና ኮፒ ተብሎ እላዩ ላይ ተጽፎበት በሁለቱም ፖስታዎች ላይ ስም ፤ አድራሻና የፕሮጀክቱ ስም በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍና በሰነዱ ላይ በመፈረም በሰም በታሸገ አንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና እላይ በተዘረዘሩ ጽሑፎች እላይ ላይ በመጻፍ ማህተም በማሳረፍና በመፈረም እንደዚሁም የቴክኒካል ሰነዱ ተሞልተው አንድ ኦርጂናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒው በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ የጨረታ ማስከበሪያ /Bid Bond/ በኦርጂናልና ቴክኒካል ሰነድ ውስጥ ተካተው ኦርጂናልና ኮፒ ተበሎ እላይ ላይ ተጽፎበት በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ሁለቱንም ማለትም የቴክኒካልና የፋናንሽያል ፖስታዎችን በትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ ተከተው እላይ ላይ በተገለጹ ዝርዝር ጹሁፍ ተጽፎበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ በ5:00 ሰዓት በቁጫ አልፋ ወረዳ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ-5 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፤
- ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ በፊት የስራ ሳይቱን በራሱ ወጪ አይቶ ያለበትን ማረጋገጫ ደብዳቤ ከቁጫ እልፋ ወረዳ ዋና አስተዳደር ጽ/ቤት እና የቦታውን ፎቶ ግራፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 21 / ሃያ አንድ/ ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንት ሰነድ የማይመለስ 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ወደ ጋሞ ዞን ቀጫ አልፋ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቀጥር-5 ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond /320,000/ (ሦስት መቶ ሃያ ሺህ ብር) ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ ህጋዊ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ተቀባይነት የለውም፡፡
- የጨረታው ሳጥን የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ስራ ቀን ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- የማንኛውም ተጫራቾች አርትሜትክ ቼክ ውጤቱ ከተነበበው ዋጋ አንጻር ከ3% በላይና በታች ሆኖ ከተገኘ ከጨረታው ውጪ ይሆናል ፡፡ በተመሳሳይ /ሪቨት/ ቅናሽ ከ10% በላይ ማድረግም ከጨረታው ውጪ ያደረጋል፡፡
- የማንኛውም ተጫራች የቀረበው ዋጋ ከመሀንድስ ግምት ከ15% በላይ እና 25% በታች ሆኖ ከተገኘ ተጫራቹ ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ: 0916669982/0926366087/0976135648/0984666189 ደውሎ ይጠይቁ፡
በደ/ኢት/ክ/ጋሞ/ዞን/ቁጫ/አልፋ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት
