Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በሐራጅ ጨረታ እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፤ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የግልፅ እና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 38/2017

 

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሸከርካሪዎችን በሐራጅ ጨረታ እንዲሁም የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፤ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ሚያዝያ 09 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ የሚታወቅ ሲሆን በተጨማሪም በግልጽ ዕቃ ጨረታ ላይ የሚሣተፉ ተጫራቾች ሰነዱን ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ባመቻቸው የበይነ መረብ (Online) የማጫረቻ ሲስተም መተግበሪያ auction.et ላይ ከላይ ከተጠቀሰው ቀን ጀምሮ የሚያገኙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በመሆኑም

  1. በተሽከርካሪ ሐራጅ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ጨረታው ከመከፈቱ አስቀድሞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
  2. በግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል ወይም በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ባመቻቸው የማጫረቻ ሲስተም መተግበሪያ auction.et ላይ በማያያዝ በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል፡፡
  3. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡
  4. ተጫራቾች የዕቃዎችን የግልፅ እንዲሁም የተሽከርካሪውን ሐራጅ ጨረታ ሠነድ ከሀሙስ ሚያዝያ 09 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ/ጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ በተጨማሪም የዕቃው የግልጽ ጨረታ ሰነድ በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ድረ ገጽ auction.et ላይ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ያገኙታል።
  5. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ/ጽ/ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. የተሽከርካሪ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለሚሳተፉባቸውን ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በተ.ቁ: 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ በአካል በመቅረብ ማስያዝ አለበት።

 

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነዱ ከወሰዱበት ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት

የእቃ ግልፅ

እስከ 14/08/2017

15/08/2017 3፡45 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 4፡00 ሠዓት ይከፈታል

የተሽከርካሪ ሐራጅ

እስከ 15/08/2017

16/08/2017 4፡00 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

 

  1. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡- አ.አ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡ እንዲሁም በበይነ መረብ (Online) የሚጫረቱ ተጫራቾች በድረ ገፁ መከታተል ይችላሉ፡፡
  2. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
  3.  አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።
  4. ከላይ በተ/ቁ 10 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረከበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
  5. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ :- 011 470 85 03 እንዲሁም የአክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-5511/ 011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ:- በዕቃ ግልጽ ጨረታ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከቀረቡት ሁለት የመጫረቻ አማራጮች መካከል በተመቻቸው በአንዱ ብቻ መጫረት የሚችሉ ሲሆን በአንድ ተጫራች ስም በሁለቱም አማራጮች መጫረት ከጨረታው የሚያስረዝ ይሆናል፡፡ በኦንላይን መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በአክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር ድረ-ገፅ መተግበሪያ auction.et መሰረት መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።

አድራሻ፡- ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፡- ሳሪስ አቦ ቤ/ክ በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

አክሽን ኢትዮጵያ፡- ቦሌ አትላስ ከለላ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢ.ቁ. 301

 

አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender