Tender Detail

Tender Details

  • Company የጨንቻ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
  • Address ደቡብ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0916881031
  • Website
  • Deadline29 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-29 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction

የጨንቻ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ለጨንቻ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ሎት (1) እና ሎት (2) የኮብል ስቶን ንጣፍና የዲች ግንባታ ፣ሎት (3) የዲች ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል

የጨንቻ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የጨንቻ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ለጨንቻ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ሎት (1) እና ሎት (2) የኮብል ስቶን ንጣፍና የዲች ግንባታ ፣ሎት (3) የዲች ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል ስለሆነም በመንግስት ግዢ አዋጅና ደንብ መመሪያ መሠረት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በጣት አሻራ የተረጋገጠ መረጃ ሰርተፍኬት /Tin No/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት /Vat ተመዝጋቢ/ ደረጃቸው ቢሲ/ጂሲ 8 ያላቸው።

  • በኮንስትራከሽን ሚኒስቴር ወይም አግባብነት ካለው መንግስት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  • ከዚህ ቀደም በዘርፉ የኮብል ስቶን ንጣፍና የዲች ግንባታ/ ቢያንስ 2 ሳይት ላይ የሰራበትን የመልካም ሥራ አፈፃጻም ልምድ ማቅረብ የሚችል::
  • የጨረታ ማስከበሪያ /CPO ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  • ማህበራትን በተመለከተ አደራጅ መ/ቤቱ ዋስትና የሚቀበልበትን በቂ መረጃ ማቅረብ አለበት ።
  • ጨረታውን ለማጉላላት/ ለማስተጓጎል ሆን ብሎ ሀሰተኛ ሰነድ ያቀረበ ለማሳሳት የሞከረ /የሚሞክሩ ተጫራቶች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ ለወደፊት ከመንግስት መስሪያ ቤት የሚወጡ ጨረታዎች እንዳይሳተፍ እንደሚደረግና የጨረታ ማስከበሪያው CPO ውርስ ይሆናል።
  • በጨረታ ሂደት ላይ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላው ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት፤
  • በግንባታ አፈፃፀም ችግር ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጠው የስራ ተቋራጭ ጨረታውን መወዳደር አይችልም።
  • ማንኛውም ተጫራች የውድድሩን ዋጋ ከመሙላቱ በፊት የሚሰራበትን ሳይት በራሱ ወጪ ተንቀሳቅሶ በማየት ስለሳይቱ በቂ እውቀት ኖሮት ለሥራው መቀላጠፍ ይረዳው ዘንድ አስፈላጊውን ማሽነሪ እና የግንባታ ግብዓት ዋጋን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የሰነዱን ነጠላ ዋጋ መሙላት ይኖርበታል::
  • የጨረታ ሰነዱ ቴከኒካልና ፋይናንሻል አንድ ኦርጂናልና ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒዎችን ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተው እና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ የድርጅቱ ማህተም በመምታት የጨረታ ሰነዱን ከፋይናንስ ጽ/ቤት ቀርቦ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ 15 የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ፤ በ16ኛው ቀን እስከ 5፡00 ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነዶቻቸውን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: በዕለቱ ልክ በ5:00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፤ በመቀጠልም በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል:: ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

 

የጨንቻ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት

 

Save Tender