ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት መለስተኛ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::
EXHIBITION CENTER & MARKET DEVELOPMENT ENTERPRISE (የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት)
ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት
EXHIBITION CENTER & MARKET DEVELOPMENT ENTERPRISE
መለስተኛ የእግርኳስ መጫወቻ ሜዳ ግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
ኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት መለስተኛ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: ስለሆነም ተጫራቾች የጨረታውን ሙሉ መረጃ የያዘውን ሰነድ ከሚያዚያ 6/2017 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 25/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት20 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ኤግዝቢሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት በመምጣት ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ::
ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ሞልተው ሚያዚያ 28/2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00-4፡30 ድረስ በማዕከሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በዚሁ ዕለት ማለትም ሚያዚያ 28 /2017 ዓ.ም ከቀኑ 4፡35 ላይ በማዕከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
ለተጨማሪ መረጃ :- 0912-01-73-78/0115-15-16-99 ላይ መደወል ይቻላል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
