በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቂልጦ ጎሞሮ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል ባለሶስት እግር የጭነት ባጃጅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቂልጦ ጎሞሮ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል ባለሶስት እግር የጭነት ባጃጅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለሶስት እግር የጭነት ባጃጅ ግዥ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል በምስ አዘ/በር/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በመምጣት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡ በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ
- የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስረከቢያው /CPO/ 15,000 ብር ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ለጨረታው ያሸነፉበትን እቃ ምስ/አዘ/በ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ የትራንስፖርት የማስጫኛና የማውረጃ ጨምሮ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቭሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በቀኑ 08፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተባለው ሰዓት ታሽጎ በተባለው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ ፋይናንሻል ዋጋዎች በግልጽና በጥራት የሚታዩና ስርዝ ወይም ድልዝ ያልሆኑ መሆን አለባቸው::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ወረዳው ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ሲሆን 176 ኪሎ ሜትር አስፓልት እና 45 ኪሎ ሜትር ፒስታ መንገድ ነው፡፡ለተጨማሪ መረጃ ስልከ ቁጥር 09 33 62 02 20/09 21 33 86 96
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልዊ መ/በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
