Tender Detail

Tender Details

  • Deadline04 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-04 00:00:00
  • Categories Building Construction

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው በንሳ ወረዳ ጎንጆዊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቀሪ ግንባታ ሥራ ለማሠራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው በንሳ ወረዳ ጎንጆዊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቀሪ ግንባታ ሥራ ለማሠራት ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት:-

  1. ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች 2017 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና - የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ኮንስትራክሽን ሚንስቴር ወይም ሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ እና የእቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው::
  2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው።
  3. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መሥሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መሥሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  4. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋናው ውል ስምምነት ገብተው ሶስትና ከዚያ በላይ ሥራ ጀምረው ያላጠናቀቁ (ያልጨረሱ) ተቋራጮች ጨረታውን መግዛት ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  5. የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና BANK GAURANTEE ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 (ለሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ።
  8. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
  9. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (አርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ ግዥ/ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
  11. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  13. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ

Save Tender