Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የዱና ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ሀዲያ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916443676
  • Website
  • Deadline28 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-28 00:00:00
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Generators , Vehicle

በሀዲያ ዞን የዱና ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ መኪና፣ ሞተር ሳይክሎች እና ጄኔሬተር ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የዱና ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሀዲያ ዞን የዱና ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ መኪና፣ ሞተር ሳይክሎች እና ጄኔሬተር ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡-

  • ሎት - 1 መኪና
  • ሎት - 2 ሞተር ሳይክሎች
  • ሎት - 3 ጄኔሬተር
  1. መኪና፣ ሞተር ሳይክሎች እና ጄኔሬተር የሚገኙበት አድራሻ በሀዲያ ዞን ዱና ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት እና በሀዲያ ዞን ዱና ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
  2. በጨረታው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።
  3. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው እየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ መኪና፣ ሞተር ሳይክሎች እና ጄኔሬተር በተናጠል፡- ሎት - 1 መኪና ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ፣ ሎት - 2 ሞተር ሳይክል ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ እና ሎት 3 ጄኔሬተር ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመክፈል በሀዲያ ዞን ዱና ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ተሽከርካሪ/ዎች በሎት በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና /Original/ እና ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 04 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፈደል በመጻፃፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፈርማ ማረጋገጥ አለባቸው ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም::
  7. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ተሽከርካሪ መጫረት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው /አስራ ስድስተኛው/ ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ8:30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ንብረት አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ በ10 /አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  10. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ወይም ንብረት ከመንግስት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  11. አሸናፊው ተጫራች መኪና፣ ሞተር ሳይክሎች እና ጄኔሬተር ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፍናል፡፡
  12. ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው::
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ መሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0916443676 / 0952123232 / 0931372049 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን የዱና ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender