Tender Detail

Tender Details

  • Company Debre Tabor University (ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ)
  • Address Debre Tabor : Ethiopia, Phone: 058 141 0526
  • Websitehttps://dtu.edu.et/
  • Deadline27 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-27 00:00:00
  • Categories Firewood

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለ2017 በጀት ዓመት ለተማሪዎች ምግብ ማብሰያ አገልግሎት የሚውል የማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Debre Tabor University (ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ለ2017 በጀት ዓመት ለተማሪዎች ምግብ ማብሰያ አገልግሎት የሚውል የማገዶ እንጨት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፦

  1. የዘመኑን ግብር የከፈለና ማስረጃ የሚያቀርብ
  2. በግዥ ኤጀንሲ በEGP በአቅራቢነት የተመዘገበ
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ተመዝጋቢ የሆነ
  4. በዘርፉ ህጋዊና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለውና ማስረጃ የሚያቀርብ
  5. እቃዎቹን በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ የሚችል
  6. የጨረታ ማስከበሪያ
  7. ለሎት 01 የማገዶ እንጨት ብር 20,000 በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ስም ማስያዝ የሚችል ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ደብረታቦር ከሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ግቢ አዲሱ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ መግዛት ይችላል።
  8. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሱ ወጭ ደብረታቦር ከሚገኘው የዩኒቨርሲቲው መጋዘን ውስጥ ማስገባት አለበት።
  9. ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሰነዶቹን መግዛት ይችላሉ። ከዚያም ከዚህ በታች በሎቱ የተሰጠውን የጨረታ ሳጥን መዝጊያ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት በማድረግ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ሞልተው ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ አስተዳደር ህንፃ ለዚህ ጨረታ ተብሎ ለየሎቶች በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  10.  የጨረታ ሳጥን አዘጋግና አከፋፈት ሥነ ስርዓትን በተመለከተ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ማንነታቸውን የሚገልጽ መረጃ ይዘው በተገኙበት፤

ሀ/ ለሎት 01 ጨረታው በዚህ ጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡10 ላይ ይከፈታል።

የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ8ኛው እስከ 15ኛው ቀን ውል ካልያዘ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም።

ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡- የጨረታው መከፈቻ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 141 0526 መጠየቅ ይቻላል።

 

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ

 

Save Tender