Tender Detail

Tender Details

  • Company በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address አረካ ከተማ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0465521713
  • Website
  • Deadline26 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-26 00:00:00
  • Categories Building Construction

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የወላይታ ዞን አረካ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዘመን በማዘጋጃ ቤት መደበኛ ፕሮግራም የሚሠሩ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ግንባታ ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

በወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የወላይታ ዞን አረካ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዘመን በማዘጋጃ ቤት መደበኛ ፕሮግራም የሚሠሩ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ግንባታ ግዢ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት:-

ሎት 1 - የአረካ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ሽንት ቤት ግንባታ ሥራ ግዥ፣

ሎት 2 - የአረካ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዙሪያ አጥር ግንባታ ግዥ ፤

ሎት 3 - የእንጨትና እንጨት ውጤቶች ግዥ፤

በዚህ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው::

  1. ለሎት 1 GC/BC-8 ሲሆን ለሎት 2 GC/BC-7 እና ከዛ በላይ የሆኑ፤
  2. ለሎት 1 የማህበራት ማደራጃ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ካደራጅ መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የ2017 ዓ.ም የንግድ ሥራ ፈቃድ ያሳደሱ፤
  4. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  5. ቲን ሠርቴፊኬት ያላቸው፤
  6. በ Online አቅራቢነት E-GP የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 - 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/፤ ለሎት 2 - 165,000 (አንድ መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ብር) እና ለሎት 3 - 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ)፤ በጥሬ ገንዘብ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና/ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ሎት 1 እና ሎት 2 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እና ሎት 3 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 600.00 /ስድስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከአረካ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት በፑል ማዕከል መግዛት የሚትችሉ መሆኑን እየገለጽን የአንዱንና ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ማቅረብ የሚቻል ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ሎት 1 እና ሎት 2 በ31ኛው ቀን፣ ሎት 3 በ16ኛው ቀን ዕለቱ የሥራ ቀን ከሆነ በ4፡00 ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች ያለመገኘታቸው የጨረታ ሂደቱን እያስተጓጉልም፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-5-52-08-00/02-41/ 09-13-05-51-85 ማነጋገር ይችላሉ፡፡

 

በወላይታ ዞን የአረካ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender