የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለዋናው መ/ቤት (የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት) የጥበቃ ስራ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Conformity Assessment Enterprise -ECAE (የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት)
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የጥበቃ አገልግሎት ግዥ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ፡ ኢ.ተ.ም.ድ /ብግጨ/ጥበቃ/004/17
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለዋናው መ/ቤት (የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት) የጥበቃ ስራ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በሥራ መስኩ ሕጋዊ የስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ በተጨማሪ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገዛበት ወቅት የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ ይዞ መቅረብ አለባቸው፡፡
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከፌዴራል ወይም ከክልል ፖሊስ ማቅረብ የሚችል፣
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነትን የምዝገባ ወረቀትና የግብር መለያ ቁጥር (Tin No.) ያላቸው መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና እንዲሁም በመንግስት መ/ቤቶች በጨረታ ለመሳተፍ እንደሚችሉ ከፌዴራል ወይም ከክልል ግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች በመንግስት መ/ቤቶች ጨረታ እንዳይሳተፉ የታገዱ መሆን የለባቸውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ድርጅቱ ዋና መ/ቤት ግዥና አቅርቦት ቢሮ ህንፃ አንድ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 304 በመገኘት ህጋዊ ሠነዶችን በመያዝ የማይመለስ ብር 700 /ሰባት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አስፈላጊ ከሆኑ የጨረታ ሠነዶች ጋር በማካተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሠነዱን በታሸገ ፖስታ አግባብ ባለው አካል በመፈረም ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ሠነዶችን በማዘጋጀት በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለብቻው በፖስታ ወይም በቴክኒካል ሠነድ ፖስታ ውስጥ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ፋይናንሺያል ፖስታ ውስጥ የተደረገ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ይታሸግና በዕለቱ በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና አቅርቦት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 16ኛው ቀን የሕዝብ በዓል የሚከበርበት ቀን ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ጨረታው ሲከፈት በቦታው ባይገኙ የጨረታ መክፈት ሂደቱን አያስተጓጉለውም፡፡
- ተጫራቶች አጠቃላይ ለዋናው መ/ቤት (የጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት) የግቢ ሁኔታ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ መመልከት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ውጤት አሸናፊ እንደታወቀ ተሸናፊ ድርጅቶች ያስያዙት ቢድ ቦንድ ወዲውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና በማቅረብ ውል ይፈራረማል፡፡
- ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻውንና ሥማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ መፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ ማህተም ያልተደረገና ያልተፈረመ ሰነድ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከማስገባታቸው በፊት የጨረታ ሠነዱን በጥንቃቄ ማንበብ ይገባቸዋል። በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡትን መመሪያዎች አለመተግበር ከጨረታው ያሠርዛል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0930630972 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ስልክ 0911679184/0930630972 ፖ.ሳ.ቁ 1145
የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት /አዲስ አበባ/
