Tender Detail

Tender Details

  • Company Sidama Football Federation (የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን)
  • Address Awassa, Ethiopia, Phone: 0462216730
  • Website
  • Deadline25 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-26 00:00:00
  • Categories

የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ስፖርት ማቴሪያሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Sidama Football Federation (የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን)


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ስፖርት ማቴሪያሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች፤

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዢ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ፤
  5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 10,000.00 (አስር ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታው በሁለት ፖስታ የሚቀርብ ሲሆን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ መቅረብ አለበት :: ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ተኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ በ10፡00 ሰአት ተዘግቶ በ3፡00 የሚከፈት ይሆናል፣
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥር ማስፈር አለባቸው፣
  7. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የግዥውን ብዛት መጠን እንደአስፈላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነስ /ለመጨመር/ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ስፖርት ዕቃ አይነት መ/ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን ዝርዝር መሰረት ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት ::
  9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0462216730 /0916155930 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የመ/ቤቱ አድራሻ ከሀዋሳ ሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፊት ለፊት

 

የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን

 

Save Tender