ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ ኮሚኒኬሽን ሥራ የሚያስፈልግ የቪዲዮ ካሜራ ከነ ሙሉ አክሰሰሪው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ ኮሚኒኬሽን ሥራ የሚያስፈልግ የቪዲዮ ካሜራ ከነ ሙሉ አክሰሰሪው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
-
-
-
-
-
-
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው::
- በፋይናንስ መሥሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና በሕግ ያልተገደቡ፡፡
- የቲን ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ያላቸው::
- ለካሜራው ግዥ ከቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት የቢሮ የግዥ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የዕቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንስ የጨረታ ሰነዱን ለብቻ ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተዘጋጀው የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ ተጨማሪ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው የኤንቨሎፑ የውጭ ገጽ ዋና ኦሪጂናል/ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በማንኛውም ኤንቨሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት የለባቸውም፤ ስለተጫራቾች የንግድ ፈቃድ፤ የቫት ሰነድ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒክ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦሪጅናል እና ኮፒ ተብሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቨሎፕ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው ኦሪጅናል/ ሆና ኮፒ ኤንቨሎፕ ውስጥ ከፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ውጪ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፡፡
- ተጫራች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በፊት ብቻ ይሆናል፡፡ ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቢሮ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡ ማንኛውም የተጫራች ሕጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በኢፌድሪ/ በክልሉ መንግሥት ሕጐች ተቀባይነት ያለው ኦሪጅናል የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፤ ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ለሚወዳደሩት ሎት ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ከታወቀ በባንክ ዋስትና የሚቀርብ በባንክ ዋስትና ለብቻው በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታውን በከፊል መጫረት የሚፈለግ ተጫራች ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች በአንድ ወይም ከአንድ በላይ መርጦ መጫረት ይቻላል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በቢሮ ስልክ ቁጥር 09-91-41-54-33 ዘወትር በሥራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
-
-
-
-
-
የቢሮው አድራሻ፡- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጎን መሆኑን ጭምር እናሳውቃለን፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ
