በከምባታ ዞን የዱራሜ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለከተማው ሴ/መ/ቤቶች ሞተር ሳይክል እና ኤሌክትሮኒክስ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
የዱራሜ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ን/አስ/ር የሥራ ሂደት ዱራሜ
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በከምባታ ዞን የዱራሜ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለከተማው ሴ/መ/ቤቶች ሞተር ሳይክል እና ኤሌክትሮኒክስ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፣
- ተጫራቾች በየዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- የአቅራቢነትና፣ የንግድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፣
ስለዚህ፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከዱ/ከ/አስ/ር/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- በወጣው የጨረታ ማስታወቂያ መሰረት ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅቶች አሸናፊነታቻው በተገለጻ በ5 ቀናት ውስጥ ውል ይፈርማሉ፤ ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ ከነቫቱ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0465541158
የዱራሜ ከተማ አስ/ር ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ን/አስ/ር የሥራ ሂደት
