አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ትራክ ማውንትድ ክሬን፣ ጠላቂ እና ሰርፌስ ፓምፖች፣ ሶላር ፓኔል፤ጀኔሬተር፣ ቫይብሬተር፣ ዲዋተሪንግ ፓምፕ፣ ኤችዲፒኢ ፓይፕ የውሃ መገጣጠሚያ እቃዎች፣ ጋቢዮን ቦክስ፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች እና የተለያዩ የኤሌክትሪክ ኬብሎችና እቃዎች ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Abay Construction (አባይ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር)
ብሄራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- አኮኃ/የተ/የግ/ማ/
ብግጨ/08/17
አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ትራክ ማውንትድ ክሬን፣ ጠላቂ እና ሰርፌስ ፓምፖች፣ ሶላር ፓኔል፤ ጀኔሬተር፣ ቫይብሬተር፣ ዲዋተሪንግ ፓምፕ፣ ኤችዲፒኢ ፓይፕ የውሃ መገጣጠሚያ እቃዎች፣ ጋቢዮን ቦክስ፣ የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች እና የተለያዩ የኤሌክትሪክ ኬብሎችና እቃዎች ግዥ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ድርጅቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
- የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 16 ድባንቄ መድሀኒያለም ቤተክርስቲያን ህዳሴ ሰፈር ታክሲ ማዞሪያ 190 ሜትር እልፍ ብሎ አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ከግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ትክክለኛ ስምና አድራሻ በመፃፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት በስራ ሰዓት ከግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይዘጋል ፤በ15ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 ይከፈታል፡፡
- 15ኛው ተከታታይ ቀን የበዓላት ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር https:/www.abayconstruction.org.et/auction-bid/ 058-3-83-04-4-60/ 09-91-02-14-30 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አባይ ኮንስትራክሽን ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
