ኦ.ቢ.ኤም (OBM) ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማህበር በገላን ከተማ ዋ/መ/ቤት ንብረት ክፍል ያለውን የተለያየ አይነት የHDPE Fitting በተቆረጠ ዋጋ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
OBM Construction S.C (ኦ.ቢ.ኤም ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማህበር)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኦ.ቢ.ኤም (OBM) ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማህበር በገላን ከተማ ዋ/መ/ቤት ንብረት ክፍል ያለውን የተለያየ አይነት የHDPE Fitting በተቆረጠ ዋጋ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የዘመኑ ግብር የከፈለ ፤ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሸህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (cpo) Cash Payment Order ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ ኮሜርስ ፊት ለፊት በሚገኘው የኦ.ቢ.ኤም ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት ቢፍቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ በመምጣት መግዛት ይችላሉ::
- የጨረታ ሰነድ አቀራረብ በ2 ኢንቨሎፕ ሆኖ፤
አንደኛው ኢንቨሎፕ ፋይናሽያል ፕሮፖዛል ክጨረታ ሰነድ ጋር በተያያዘው ሰነድ መሰረት የሚቀርብ የዋጋ ማቅረቢያ ፕሮፖዛል የያዘ ይሆናል::
ሁለተኛው የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በድርጅታችን ትክክለኛ ስም የኦቢኤም ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማህበር ስም የተዘጋጀና የመሳሰሉ ማስረጃዎችን ወዘተ…የያዘ ይሆናል:: በዚህ ዓይነት ተያይዞ ያልቀረበ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዚያ 21/08/2017 ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ ከጠዋቱ 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
- አክሲዮን ማህበሩ /ድርጅቱ/ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
አድራሻ ፡- ኦ.ቢ.ኤም ኮንስትራክሽን አ.ማ
ስልክ ቁጥር 0118-36-20-24, 0115621296
