ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የይ/ዓለም ከተማ ውሃ አገ/ድርጅት የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች ዋጋ አወዳድሮ በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል ።
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የይ/ዓለም ከተማ ውሃ አገ/ድርጅት
የጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የይ/ዓለም ከተማ ውሃ አገ/ድርጅት የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎች፡-
- የኤሌክትሪክ ዲናሞች ብዛት————6
- ፔዳል ባይስክል ብዛት————6
- ሞተር ሳይክሎች ብዛት————2
- የቧንቧና የተለያዩ ብረታ ብረቶች
- ፕላስቲኮች ዋጋ አወዳድሮ በጨረታ መሸጥ ይፈልጋል በመሆኑም እቃዎቹን መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- ለሽያጭ የቀረቡ ዕቃዎችን ሁኔታ በተመለከተ በድርጅቱ ጽ/ቤት ግቢ በአካል ቀርቦ መመልከት ይችላሉ ፤
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ የእቃዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ ሰነድ ይ/ዓለም ከተማ ውስጥ ከሚገኝው የውሃ አገ/ድርጅት ጽ/ቤት ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በተጠቀሱት ቀናቶች ዉስጥ ተጫራቾች ለሚፈልጉት ዕቃዎች ዋጋ በመሙላትና በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛዉ ቀን ከቀነ 8፡00 ድረስ ይ/ዓለም ከተማ በሚገኝው ውሃ አገ/ድርጅት ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በውሃ አገ/ድርጅት ጽ/ቤት ይሆናል ፡።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበረያ አጠቃላይ ለእቃው የሰጡት ዋጋ 5% CPO ማስያዝ ይኖርበታል፤
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ በተሰጠው ቀን ገደብ ክፍያ ፈፅሞ የማይረከብ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለውሃ አገልግሎቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ላሸነፉበት እቃ ውጤቱ ከተለጠፈበት ቀን አንስቶ ከ5 ቀናቶች በኋላ ሙሉ ገንዘብ በመክፈል እቃውን ሙሉ በሙሉ ያነሳል ፤
- ውሃ አገልግሎቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ይ/ዓለም ከተማ ውሃ አገ/ድርጅት
