በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው ሎት1 ተቋርጦ የነበረ የአስ/ር ህንፃ ግንባታ በከፊል ሎት2 የእንስሳት ክሊኒክ ግንባታ ሎት3 የመንገድ ዲዛይን ስራ በግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት (ማሰራት) ይፈልጋል::
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን ፃ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው ሎት1 ተቋርጦ የነበረ የአስ/ር ህንፃ ግንባታ በከፊል ሎት2 የእንስሳት ክሊኒክ ግንባታ ሎት3 የመንገድ ዲዛይን ስራ በግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት (ማሰራት) ይፈልጋል:: ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን
- በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- ከላይ ላሉ የግንባታ ስራዎች ሎት 1 ከደረጃ 5 ጀምሮ እና ሎት 2 ከደረጃ 8 ጀምሮ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ /1%/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው::
- ሙሉ የስራ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኝት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ሰነዱን ገንዘብ ጽ/ቤት ላይ መግዛት ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ፃ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 4:00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን 4:00 ሰአት ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ላይየሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በወረዳው ፃ/ወ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 2003 ተግባራዊ ይደረጋል::
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ
ኽምራ ዞን ፃ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት
