በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት ፖስተር እና እስቲከር ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2017 ዓ.ም
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ በ2017 በጀት ዓመት ፖስተር እና እስቲከር ህትመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በላይ የተገለጹትን ህትመቶች በውድድር ለመሳተፍ የምትፈልጉ ማሟላት ያለባችሁ፡-
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድና TIN NO ቁጥር ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው::
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙነት በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ይታሸግና ወዲያውኑ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች 15% VAT ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ተጫራች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶች ለይተው በሁለት ፖስታ በማድረግ በሰም ታሽጎ ማቅረብ አለባቸው::
- የሚቀርበው ዋጋ ከላይ የማወዳደሪያ ሀሳብ ማቅረቢያ አንቀፅና ሁኔታ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት።በተጨማሪም አሸናፊው ተጫራች የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በሃገር ውስጥ ገበያ አነስተኛ ዋጋ ላሣዩ ግዥዎች ላወጣው ጠቅላላ የውል ሁኔታዎች መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- የቀረቡት የማወዳደሪያ ሃሳቦች በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ፀንቶ የሚቆዩ ማስተካከያ የማይደረግባቸው መሆናቸውን እናረጋግጣለን፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ከሚያቀርቡት ሽያጭ ዋጋ 2% ብር ከባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በኤጀንሲው ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይቻላል፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆን በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ከዚህ የመወዳደርያ ሀሳብ ማቅረቢያ ጋር የተያያዘ የቀረበ ተጨማሪ ሠነድ የተጫራቾችን ፈርማና ማህተም ይፈልጋል፡፡ የጨረታ ሠነድ ላይ ያሉ ሁኔታዎች ከሁሉም በላይ በመወዳደርያ ሀሳብ ማቅረቢያ የቀረቡትን ሌሎች ተጨማሪ ማረጋገጫዎች ፊርማና ማህተም ካልተደረገባቸው የቀረበው ማወዳደሪያ ሀሳብ ይሰረዛል፡፡
አድራሻ፡- በኢምግረሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጎን/ ሀዋሳ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 046-2-12-02-55/ 09-16-51-69-08
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጂንሲ
