የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የቪዲዮ ካሜራ ግዥ ለመፈፀም በታቀደው መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡:
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የቪዲዮ ካሜራ ግዥ ለመፈፀም በታቀደው መሰረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡: በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ቢድ ቦንድ ወይም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በመጠቀም ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ3፡15 ሰዓት በሀዋሳ ከተማ አስ/በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ ቀን በ3፡15 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በ3፡45 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር:- 046-2-20-99-63/046-2-12-13-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ል⁄ መምሪያ
