በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር መንገድ ለማሰራት እና ባለ አራት ክፍል ሁለት ብሎክ መዋለ-ህፃናት ት/ቤት ግንባታ ለማከናወን ደረጃ 6 ፤ 7 እና በላይ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የሆነ በዚሀ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግልፅ ጨረታ ቁጥር ፡- 03/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር፦
- ለተንታ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በመደበኛ ካፒታል በጀት ከ01 ያመድ ቀበሌ ጮስ እስከ ሰንጎላ ቀበሌ ማዕከል 5.6 ኪ.ሜ መንገድ ለማሰራት በሮድ ኮንስትራክሽ እና በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 6 እና በላይ ፈቃድ ያላቸውን፤
- ለተንታ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት በአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ በጀት በአጁባር ከተማ ለሚያስገነባው ባለ አራት ክፍል ሁለት ብሎክ መዋለ-ህፃናት ት/ቤት ግንባታ ማንኛውንም የሚገነባበትን ማቴሪያል ኮንትራክተሩ ችሎ ደረጃ 7 እና በላይ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ በዚሀ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ለመንገድ እና ለመዋለ-ህፃናት ት/ቤት ግንባታ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻልን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት ሰርተፊኬት/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል የ6 ወር የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው::
ከዚህ በላይ ከተራ ቁጥር 1 - 6 የተገለፀውን መረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የግዥ መጠኑ ብር 10,000 እና በላይ ከሆነ 2% ለመንግስት /Withholding Tax/ የሚከፍሉ መሆኑን ይወቁ፡፡
- የሚሰራው የስራ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለእያንዳንዱ ስራ የጨረታ ሰነዙ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ፡11፡30 ሰዓት ድረስ ከተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ስራ ለመንገድ ስራ ብር 60,00 /ስልሳ ሺህ ብር/ ለመዋለ-ህፃናት ግንባታ ብር 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያ ያላስያዘ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በ22ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት በ4፡15 ሰዓት ላይ በይፋ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱ ላይ የሚሞሉትን ነጠላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለው ግልፅና የማያሻማ መሆን አለበት፤ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱ የሚታሸግበትን ፖስታ ጨምሮ በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ገፆች ላይ የጨረታውን ዓይነት፣ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በጥንቃቄ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች አንድ ኦሪጅናልና ኮፒ የጨረታ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በኦሪጅናልና ኮፒው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ገዥው ኦሪጅናሉ የጨረታ ሰነድ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ቀን በኋላ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለመንገድ ስራ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ከመሙላታቸው በፊት የሚሰራውን መንገድ ቦታው ድረስ በመሄድ ማየት ይችላሉ፡፡
- ለመንገድ ስራ አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈውን የመንገድ ስራ ለውለታ ሲመጣ የማሽነሪ አከራይ ተከራይ ውል ማቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በበዓላት ቀን፣ ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ስለ ጨረታው ማብራሪያ ለመጠየቅ ተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 033-4-41-05-73/ 033-4-41-02-67 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የተንታ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
