Tender Detail

Tender Details

  • Company በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል
  • Address ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-226-0373
  • Website
  • Deadline27 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-27 00:00:00
  • Categories Construction Works

በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት የለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የሕንፃ ዕድሳት ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት የለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የሕንፃ ዕድሳት ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ደረጃቸው GC-6/BC-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮች 2017 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ወይም ከሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው::
  3. በሲዳማ ክልል ውስጥ ሶስት (3) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶችን ውል ገብተው ግንባታ እያከናወኑ ያሉ እና ያላስረከቡ ስራ ተቋራጮች ይህን የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  4. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  5. የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክከለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANTEE/ ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፤
  7. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፈቃዳቸውን እና ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ/ ፋይናንስ ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  8. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታውን ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
  9. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) ፣ ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ቅጂ (ኮፒ) እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (አሪጅናል) እና ሁለት ቅጂ (ኮፒ) ሰነዶችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽገው በአንድ ትልቅ ፓስታ ውስጥ ተከትተው በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ/ፋይናንስ ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
  11. አሠሪው መሥሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
  12. አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል።
  13. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የለኩ ጠቅላላ ሆስፒታል

ለኩ

 

Save Tender