Tender Detail

Tender Details

  • Deadline06 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-06 00:00:00
  • Categories Building Construction

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕ/ክ/ መንግስት በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮ/ል/ጽ/ቤት የወረዳውን አስተዳደር ህንጻ ግንባታ ሥራ ለማሠራት ጨረታ እንዲወጣ የካፋ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በቁጥር 3502/14-15 በቀን 2/7/2017 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ መሠረት በGC ወይም በBC የደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸውን ብቁ እና ህጋዊ የግንባታ ድርጅቶች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 008/2017

 

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕ/ክ/ መንግስት በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮ/ል/ጽ/ቤት የወረዳውን አስተዳደር ህንጻ ግንባታ ሥራ ለማሠራት ጨረታ እንዲወጣ የካፋ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በቁጥር 3502/14-15 በቀን 2/7/2017 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ መሠረት በGC ወይም በBC የደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸውን ብቁ እና ህጋዊ የግንባታ ድርጅቶች አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ህጋዊ የሆነ የደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የሆነ የግንባታ ስራ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣
  2. በመንግስት መ/ቤቶች በአቅራቢነት ስለመመዝገቡ የሚያስረዳ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፤
  4. የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  5. ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነድ ለእያንዳንዱ ቢያንስ ሁለት ሁለት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኮፒ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
  6. ተጫራቾች የመልካም ሥራ አፈጻጸም ሲያቀርቡ ለእያንዳንዱ ተግባር መረጃውን ከአሠሪው መ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የብር 300,000 /ሦስት መቶ ሺህ ብር/ CPO/ በሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ስም አሠርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው ለ30 ተከታታይ ቀናት ብቻ ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ እየከፈሉ ከሺሾ እንዴ ወረዳ ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ 5. ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ገዝተው መውሰድ ይችላሉ።

የጨረታው ፖስታ ጨረታው በታወጀበት በ31 ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በእለቱ ከሰዓቱ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ ተጫራቾች ከህጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሰነድ የመክፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም::

የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ይሆናል፣ ማሳሰቢያ፦ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0476680200 መጠየቅ ይችላሉ።

 

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/በካፋ/ዞን ሺሾ-እንዴ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት

 

Save Tender