Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Tourist Trading Enterprise (የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት)
  • Address 22 Mazoriya, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011-6-61-09-95
  • Websitehttps://www.ette.com.et/
  • Deadline20 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-20 00:00:00
  • Categories

የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ እስክራፐ ብረታ ብረቶችና የብረት ውጤቶችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ ለአቅላጭ ፋብሪካዎች ብቻ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Ethiopian Tourist Trading Enterprise (የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት)


 

የተለያዩ እስክራኘ ብረታ ብረቶችን ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 01/2017

 

የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ እስክራፐ ብረታ ብረቶችና የብረት ውጤቶችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ ለአቅላጭ ፋብሪካዎች ብቻ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

የሚገኙበት ቦታ

መለኪያ

ብዛት በግምት

የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/

የጨረታ መዝጊያ ቀን

የጨረታ መክፈቻ ቀን

1

እስክራፕ ብረታ ብረቶችና የብረት ውጤቶች

አያት ደራርቱ አደባባይ ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ እና ብስራተ ገብርኤል ፊት ለፊት የድል ገበያ አዳራሽ ግቢ

በኪ.ግ

150,000.00

100,000.00

ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት

ሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት

 

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ የብረታ ብረት አቅላጭ ፋብሪካ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት 22 ማዞሪያ በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ከፍለው የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  2. የጨረታ ሰነዱን የዙ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የብረታ ብረት አቅላጭ ፋብሪካ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ጨምሮ ከተዛማጅ ማስረጃዎቻቸው ጋር በኤንቨሎፕ ታሽጎ በድርጅቱ ዋናው መ/ቤት በግዥ፣ንብረት አስተዳደርና ቴክኒክ ዳይሬከቶሬት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
  4. የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ቴክኒክ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  5. ተጫራቾች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበትን ቅጽ ሞልተውና ፈርመው ከመወዳደሪያ ስነዶቻቸው ጋር ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው። እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም።
  6. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠቃሎ በመክፈል እስክራፕ ብረታ ብረቶችና የብረት ውጤቶችን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለበት።
  7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፦ 011-6-63-68-11 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 

የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት

 

Save Tender