በላሊበላ የጥናት ዲዛይንና ቁጥጥር ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ለ2017 ዓ/ም (እኤአ 2025) በጀት አመት የተለያዩ የግድብ ፕሮጀክቶች ላይ በሪግ ለማስቆፈርና ፓከር (Packer Test) ለማሰራት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Lalibela Study Design & Supervision Works PLC (የላሊበላ የጥናት፤ የዲዛይን ቁጥጥር ስራ/ኃላ/የተ/የግል ማህበር)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር - LSD/16/002/3770/2017
በላሊበላ የጥናት ዲዛይንና ቁጥጥር ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ለ2017 ዓ/ም (እኤአ 2025) በጀት አመት የተለያዩ የግድብ ፕሮጀክቶች ላይ በሪግ ለማስቆፈርና ፓከር (Packer Test) ለማሰራት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ መግዛትና መወዳደር እንድትችሉ ተጋብዛችኋል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ከሆኑ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- በስሙ የታተመ ደረሰኝ ያለው፤
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- የአገልግሎቱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚቻል ሲሆን አቅራቢ ድርጅቱ ከላይ የተገለጹትን መስፈርቶችን ማሟላት የሚገባው ሆኖ በተዘረዘሩት “የግድብ ቦታዎች ላይ በሪግ ለማስቆፈርና ፓከር ቴስት (Packer Test) ለማሰራት የሚያስችል ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ያሟላ እና በዋጋ መሙያው ላይ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ሞልቶ በሚያቀርበው ዝቅተኛ ዋጋ መሰረት በማድረግ አሸናፊው የሚለይ ይሆናል፡፡
- የዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ስርዝ/ድልዝ ካለውም በአቅራቢው በኩል ከተሰረዘው ጎን መፈረም ይገባዋል፡፡
- አቅራቢው የነጠላ ዋጋውን በእቃው ብዛት አባዝቶ ጠቅላላ ዋጋውን ካልሞላ የነጠላ ዋጋው ተይዞ ጠቅላላ ዋጋው ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ለኩባንያው ጥቅም ሲባል ከነጠላ ዋጋው ይልቅ ጠቅላላ ዋጋው (ጥቅል ዋጋው) አዋጭ ሆኖ ካገኘው ጠቅላላ ዋጋውን (ጥቅል ዋጋውን) መውሰድ ይችላል ወይም ለኩባንያው ጥቅም ሲባል ከጠቅላላ ዋጋው (ከጥቅል ዋጋው) ይልቅ ነጠላ ዋጋው አዋጭ ሆኖ ካገኘው ነጠላ ዋጋውን መውሰድ ይችላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በላሊበላ የጥናት ዲዛይንና ቁጥጥር ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ገንዘብ ያዥ ህንጻ 03 ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለኩባንያው ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ከሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ፋይናንሻልና ቴክኒካል አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ እና ከሁለቱም ፖስታዎች ላይ የኩባንያውን ሙሉ አድራሻ ከስልክ ቁጥሩ ጋር እንዲሁም የተወዳዳሪውን ሙሉ አድራሻ ከስልክ ቁጥሩ ጋር በመጻፍና የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ በላሊበላ የጥናት ዲዛይን እና ቁጥጥር ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በኢትዮጵያ አቆጣጠር እስከ ቀኑ 11፡30 ሥዓት ድረስ መቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም በራሳቸው ጊዜ ባይገኙም በላሊበላ የጥናት ዲዛይንና ቁጥጥር ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ህንጻ ቁጥር 01 ቢሮ ቁጥር 001 በ10ኛው የሥራ ቀን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ይታሸግና በሚቀጥለው የሥራ ቀን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ወደሚቀጥለው የሥራ መጀመሪያ ቀን በማዛወር ከላይ በተገለጸው ተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጋችሁ በላሊበላ የጥናት፣ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራ/ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ህንጻ ቁ. 01፤ ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583200241/0583201366 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የኩባንያው አድራሻ፡- ላሊበላ የጥናት፤ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ባህር ዳር ቀበሌ 16 ዶክተር አዛናው ህንጻ ወይም መሪጌታ ጥላሁን የባህል ህክምና ማዕከል ወይም ባህርዳር አካዳሚ ጀርባ፡፡
ስልክ ቁጥር 058-320-02-41/058-320-13-66 ፋክስ ቁጥር 058-320-43-39 ባህርዳር/ኢትዮጵያ
የላሊበላ የጥናት፤ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራ ሃላ/የተ/የግል ማህበር
