Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔ/ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ሲዳማ
  • Address ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-2127-875
  • Website
  • Deadline19 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-19 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services

የሲዳማ ብሔ/ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ቋሚ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብሔ/ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ሲዳማ


 

የብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሲዳማ ብሔ/ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ቋሚ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ኮሚሽኑ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚያስፈልጋቸው የተለያዩ ቋሚ ተገጣጣሚ የቢሮ ፈርኒቸሮች ዕቃዎች ዝርዝር፡-

 

ተ.ቁ

የዕቃው ዓይነት

መለኪያ

ብዛት

1

Executive Table / Managerial table/

በቁጥር

2

2

Rectangular wooden office table

በቁጥር

20

3

Wooden file storage cabinets for office home

በቁጥር

10

4

Office mix mesh back chair task operators chair with headrest

በቁጥር

20

5

Office full mesh back chair task operators chair with headrest

በቁጥር

10

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

  1. በሚወዳደሩበት መስክ ለ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ማስረጃ ያላቸው፤ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ፤ ከመንግስት ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸውና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ።
  2. ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠየቀውን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታ ከሚያቀርበው መረጃ ጋር ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ እንደፍላጎታቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1.2 % የያዘ ሲፒኦ/ CPO/ በባንክ የተረጋገጠ ቼከ ፤ እንዲሁም ጥሬ ገንዘብ በማያያዝ ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ከሞሉ በኋላ የጨረታውን ሠነድ አንድ ኦርጂናል ቴክኒካል እና አንድ ፎቶ ኮፒ ቴክኒካል እንዲሁም አንድ ኦርጂናል ፋይናሽያል እና አንድ ፎቶ ኮፒ ፋይናንሽያል በማለት በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው እንደገና በአንድ ትልቅ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው በኤንቨሎፑ ላይ የተጫራቾች ድርጅት ማህተም አርፎበት በሰም ታሽጎ ፖስታ እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ወደ ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. በዚሁ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ከታሽገ በኋላ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በኮሚሽኑ ግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል።
  6. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ እለት ናሙና ማቅረብ አለበት።
  7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት /15 / ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታውን ሰነድ የኢትዮጵያ ብር /100/ አንድ መቶ / በመክፈል ከግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ።
  8. የሚቀርበው የዕቃ ዓይነትና ብዛት በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ የተዘረዘረ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ መመሪያውን በሚገባ በማንበብ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር ማብራሪያ የያዘ ስለሆነ ይበልጥ ተቀባይነት ይኖረዋል።
  9. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነታቸው ከተገለፀ ጊዜ ጀምሮ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መግባት ይኖርባቸዋል። ውል የማይገቡ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረስባቸዋል።
  10. ኮሚሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-2127-875 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

 

የሲዳማ ብሔ/ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ሲዳማ

 

Save Tender