የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሀረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Supply and fix 800 kva generator ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-DCE/SF/81/2025
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሀረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Supply and fix 800 kva generator ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
የፕሮጀክቱ ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
|
1 |
Supply and fix 800 kva generator |
ለሀረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል አፓርትመንት
|
DCE/SF/81/ 2025
|
ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ሚያዚያ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት
|
100,000.00 |
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ (Bid Bond) ለ120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋጠ ቼክ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የመድን ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ምርት (ብራንድ) ብቻ ነው፡፡ በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ትምህርት ቤት አጠገብ (ቃሊቲ ቶታል አዲሱ ስታዲየም ጀርባ) አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ (ቃሊቲ ቶታል አዲሱ ስታዲየም ጀርባ) እንገኛለን፡፡
የቀጥታ ስልክ ቁጥር፡-011-440-3434
ማዞሪያ፡-011-442-2270/71/72
ፖ.ሳ.ቁ፡-3414 ፋክስ ቁጥር፡-011-440-0471/ 011-442-0746
የድረ-ገፅ አድራሻ፡- www.dce-et.com
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
