በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለሚያስገነባው ንብረት ክፍል ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለሚያስገነባው ንብረት ክፍል ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡-
- በኮንስትራክሽን ሚኒስተር የተመዝገቡ፤ ደረጃቸው GC/BC-6 ና ከዛ በላይ የሆኑ፤ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና በ2017 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ ተ.እ.ታ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ከሚመለከተው ከፍል የተሰጠ ታክሲ ክሊራንስ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የአንድ ዓመት ታክስ ከሊራንስ /TAX CLEARANCE / ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከአሠሪ መ/ቤት የተሠጠ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ከ2014ዓ.ም ጀምሮ ቢያንስ ሶስት የሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ ሆነው የመልካም ሥራ አፈጻጸም የመጨረሻ ዙር ክፍያ ሰርቴፍኬት፤ የጊዜያዊ ርክብክብ ቨርቫል ወይም የመጨረሻ ርክብክብ ቨርቫልና የሥራ ውል ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዶክመንቱ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺ ብር) በመክፈል ጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 የንግድ ፈቃዳቸውን ዋናውን /Original / በመያዝ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ /CPO/ 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናሉን ለየብቻ በአንድ እናት ፖስታ ላይ በማሸግና 2 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መከተት ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው ሳጥኑ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ክፍት ሆኖ ውሎ በ22ኛው ቀን 3:30 ሰዓት ታሸጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4:00 ሰዓት ጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል:: 22ኛው ቀን በዓል ወይም የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል ማለት ነው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም::
- ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ንባብና በሂሳብ ማስተካከያ ዩነት 2% በላይና በታች መሆን የለበትም።
- ተጫራቾች በዞኑ ውስጥ ሲሠሩ ምንም ዓይነት ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው መሆን አለባቸው፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ 09 13 32 97 28 ይደውሉ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጎፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
