ሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው የግቢ ማስዋብ፣ የአዳራሽ ጥገና፣ የዶሮ ቤት የፋውንቴን የሞተር ሳይክል ማቆሚያ ስፍራ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው የግቢ ማስዋብ፣ የአዳራሽ ጥገና፣ የዶሮ ቤት የፋውንቴን የሞተር ሳይክል ማቆሚያ ስፍራ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት-
- ደረጃቸው GC-6/BC-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮች በ2017 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No ) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ወይም ከሲዳማ ከልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የታደስ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀከቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋናው ውል ስምምነት ገብተው ሶስትና ከዚያ በላይ ሥራ ጀምረው ያላጠናቀቁ (ያልጨረሱ) ተቋራጮች ጨረታውን መግዛት ሆነ መወዳደር አይችሉም።
- የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፣ ይህ ተጣርተው ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትከከለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያው (bid sccurity) ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (BANK GUARANTEE) ወይም ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፣
- የሥራ ተቋራጮቾች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.ዕ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ስም በባንክ አካውንት ቁጥር 1000337749678 በማስገባት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 005 በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የሥራ ተቋራጮቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው::
- የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የጨረታ ማስከበሪያ (bid bond security) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተው እና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሽግ አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተገለጸው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
- አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ
