Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian sugar industry group Omo kuraz 1 & 3 Sugar Factory (በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት)
  • Address አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል በሚያስገባው አስፓልት ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነበ ወርቅ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ 3 ቁጥር ማዞሪያ / ቶታል ገባ ብሎ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 251910120628
  • Website
  • Deadline23 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-23 00:00:00
  • Categories Spare Parts

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የMechanical መለዋወጫዎች (Bearing, Seal and Belt) እና የፋብሪካ የወርክ-ሾፕ እቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian sugar industry group Omo kuraz 1 & 3 Sugar Factory (በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት)


 

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ LP/OT/011/OKSF1&3/2017

 

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት የተለያዩ ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ የMechanical መለዋወጫዎች (Bearing, Seal and Belt) እና የፋብሪካ የወርክ-ሾፕ እቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ/አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን/መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ/መረጃ ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

አድራሻ ፡- ኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ የግዥ ቡድን አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ቢሮ ወደ አየር ጤና በሚወስደው ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ ወደ ተዘንኣ አጠቃላይ ሆስፒታል በሚወስደው አስፋልት የፌደራል ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ የቢሮ ቁጥር 1371/125 ነው።

የስልክ ቁጥር +251910120628/+251-913544731/+251-916170834

አዲስ አበባ

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ የፋብሪካ የMechanical መለዋወጫዎች (Bearing Seal and Belt) እና የፋብሪካ የወርክ ሾፕ እቃዎች የተመለከተውን የብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

* ሎት-1 የ Electrodes, cutting and Grinding disc ግዥ 50,000 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር ከ00/100 ሳንቲም)

* ሎት-2 የ Mechanical, Electrical and Field equipment Maintenance Consumables material ግዥ 50,000 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር ከ00/100 ሳንቲም)

* ሎት-3 የMechanical Tools and tackles, workshop tools and Electrical and Instrumentation tools ግዥ 50,000 ብር (ሃምሳ ሺህ ብር ከ00/100 ሳንቲም)

ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በ15/8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን በ15/8/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

4. የጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው።

5. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ 90 ቀናት ነው።

ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩኘ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ

 

Save Tender