Tender Detail

Tender Details

  • Company የደ/ማ/ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል
  • Address ደ/ማርቆስ ከተማ አምባሰል ህንጻ 5ኛ ፎቅ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 058-178-10-73
  • Website
  • Deadline18 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-18 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Stationery Materials

በአብክመ የሙያ ብ/ም/ማ/ኤጀንሲ የደ/ማ/ከ/ማዕከል ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽዳት እቃዎች እና ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የደ/ማ/ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር ማዕከል


 

 ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ የሙያ ብ/ም/ማ/ኤጀንሲ የደ/ማ/ከ/ማዕከል ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የጽዳት እቃዎች እና ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡

4. የግዥው ጠቅላላ መጠን ዋጋ ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ /ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የሚገዙ እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከክላስተሩ ግዥ ኦፊሰር በነፃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋና ገንዘብ ያዥ ላይ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደ/ማ/የሙ/ብ/ም/ማ/ክ/ ማዕከል ግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 5፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

 10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት 16ኛው ቀን በ 8፡00 ሠዓት ይከፈታል፡፡ ካልተገኙም በኮሚቴው ይከፈታል/ ነገር ግን 16ኛው ቀን የበአል ቀን ከሆነ ሰአቱ እንደተጠበቀ የጨረታ ማስገቢያና መክፈቻ ቀን በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል፡፡

11. ተጫራቾች ከላስተሩ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የእቃውን ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከተቀመጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም፡፡

12. የጨረታው ውድድር የሚታየው ከላስተሩ ባወጣው ዝርዝር መሰረት በጥቅል ዋጋ /በሎት/ ይሆናል፡፡

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. በጨረታ የሚሳተፉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁ/ 058-178-10-73 / 058 178 6012 / በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ 

አድራሻ፡- ደ/ማርቆስ ከተማ አምባሰል ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡

 

የደ/ማ/ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ

ክላስተር ማዕከል

  

Save Tender