Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት አዲሱ የውርስ መጋዘን ቅጥር ግቢ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462125896
  • Website
  • Deadline16 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-16 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Office Supplies And Services

በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

 የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ መንግስታዊ ግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ የተመዘገቡ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቲ.ኦቲ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈለ ሆኖ እነኝህን ማስረጃዎችን አደራጅተው ማቅረብ የሚችሉ፡-

  • ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000013485236 በማስገባት 4ኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 46 በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በCPO በባንክ የተረጋገጠ ካቀረቡት አጠቃላይ ዋጋ ከ.ተ.እ.ታ/ቲ.ኦ.ቲ በፊት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

  • ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀን አየር ላይውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት 4ኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።

  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ዋናውንና አንድ ኮፒ እና ፋይናሻል ዋናውንና አንድ ኮፒ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም የታሸገ ፖስታ በማድረግ 4ኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡

  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን እሑድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል። ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046-220-42-24/046-212-34-68 ይጠቀሙ።

አድራሻ፦ ወንዶ ንግድና እንቨስትመንት ቢሮ አጠገብ።

 

በገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት

  

Save Tender