Tender Detail

Tender Details

  • Deadline16 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-16 00:00:00
  • Categories System Supply And Installation

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጃንሜዳ ሰላም ማስከበር G+3 እና ለሀገር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ lightning preventer እና lighting arrester systems ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። 


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፡- DCE/EM/76/2025 እና DCE/EM/77/2025 

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጃንሜዳ ሰላም ማስከበር G+3 እና ለሀገር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ lightning preventer እና lighting arrester systems ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። 

 

No.

የዕቃው ዓይነት 

ፕሮጀክት

የጨረታ ቁጥር

የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ በብር

1

Lightning preventer

ጃንሜዳ ሰላም ማስከበር G+3

DCE/EM/76/2025

ሚያዝያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት

ሚያዝያ 8 ቀን 2017 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት 

50,000

2

Lighting arrester systems 

ለሀገር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፖርትመንት

DCE/EM/77/2025

ሚያዝያ 8 ቀን 2017 በ4፡15 ሰዓት

ሚያዝያ 8 ቀን 2017 በ4፡30ሰዓት

50,000

 

ስለሆነም ፡-

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማሰረጃ እና በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

  2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረገቦ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ (Bid Bond) 120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠ የተረጋጠ ቼክ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የመድን ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።

  3. አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ምርት (ብራንድ) ብቻ ነው፡፡ በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

  4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ትምህርት ቤት አጠገብ (ቃሊቲ ቶታል አዲሱ ስታዲየም ጀርባ) አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት ግዥ ቡድን ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡

  6. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

 

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ 

የቀጥታ ስልክ ቁጥር፡- 011-4-40-34-34 

ማዞሪያ :- 011-4-42-22-70/71/72

ፖ.ሳ. ቁ 011-4-40-04-71/011-4-42-07-46

አድራሻ፡- በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ትምህርት ቤት ለጠገብ (ቃሊቲ ቶታል አዲሱ ስታዲየም ጀርባ) እንገኛለን፡፡

ድረ-ገፅ:-www.dce.et.com

 

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

 

Save Tender