በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች 06 እና 07 ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማ/ጽ/ቤት
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት በተለያዩ ወረዳዎች 06 እና 07 ለሚያሰራቸው የግንባታ ስራዎች በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፤ የተሟላ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችሉ እና የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
|
ተራ ቁጥር |
የፕሮጀክት ስም |
ወረዳ |
የጨረታ ዋስትና ብር መጠን |
የተቋራጭ ደረጃ |
የአማካሪ ደረጃ |
ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ |
|
ተቋራጭ |
||||||
|
1 |
የኮሪደር ልማት (የእግረኛ መንገድ) የቴራዞ ስራ |
06 |
ለደረጃ 6 እና ከዛ በላይ 300,000 ብር |
ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ የሆነ |
||
|
2 |
የኮሪደር ልማት (የእግረኛ መንገድ) የቴራዞ ስራ |
07 |
-
ለስራው ንግድ ምዝገባና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የ2016 ዓ.ም የከፈሉ የ2016 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ከፌደራል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እንዲሁም በ2017 በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው (supplier list) ፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው::
-
ተጫራቾች የጨረታው ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦርጂናል ሁለት ኮፒ እና ፋይናሻል አንድ ኦርጂናል ሁለት ኮፒ በማሸግ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ፊርማ ፤ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND or BID SECURITY) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን 3 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም ፤ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የፕሮጀክት ስም በመጻፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይንም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡
-
ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት (Calendar Days) የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ሽያጭ ዘወትር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 402 ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት መሰረት ልማት በተራ ቁጥር 3 የተጠቀሱት ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው የመቁጠሪያ ቀን (Calendar Days) ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ማሳሰቢያ ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ያለው 11ኛው የሥራ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሰራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
-
ተጫራቾች ለ90 ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) በባንክ ትእዛዝ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE/ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት ስም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
-
ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋን ያላገናዘበ እጅግ የተጋነነ ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ የሚሰራውን ሥራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቹ የዋጋ ትንታኔ (Cost Break down) ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከሥራው ጋር ያልተመጣጣነ (unbalanced rate) ከሆነ ተጫራቹ ከጨረታ ውድድሩ ውጪ ይደረጋል፡፡
-
ተጫራቹ ለጨረታ ያስገባው ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ (Unsigned Rate Correction) እና ነጠላ ዋጋው ላይ ፍሉድ መጠቀም (to use fluid for Rate Correction) ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
-
በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ አለመሙላት (unfilled rate) ከተገኘ ስራውን በነጻ እንደሚሰራ ይወሰዳል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የተጫራቾች መመሪያ በሚያዘው መሠረት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
በወጣው ጨረታ ላይ የሚወዳደሩት ተጫራቾች ቢያንስ አንድ የኮሪደር ልማት መስራታቸውን የሚያረጋግጥ ስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
-
ስራውን ለመስራት ቀንም ማታም መስራት የሚችል፤
-
ክፍያውን በተመለከተ በራሱ ወጪ መስራት የሚችል እና ክፍያ የሚጠይቀው ስራው 60% ሲደርስ መጠየቅ የሚችል፡፡
-
እጃቸው ላይ ምንም አይነት ስራ እንደሌላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ስራም ካላቸው 80% መድረሱን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
-
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ ፡-
-
አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በመረጠው አንድ ሎት ብቻ ይሆናል። ከአንድ ሎት በላይ ተወዳድሮ የተገኘ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
-
የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 402 ህ/ተ/በጎ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት መሰረት ልማት ቡደን በጽሑፍ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ።
አድራሻ ቤቴል ፖስታ ቤት
ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማ/ጽ/ቤት
