Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-13 00:00:00
  • Categories Engineering Consultant

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የዋና መ/ቤትና ደብረዘይት ማሰልጠኛ ተቋማቱ ላይ የሚሰሩ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ጥናትና ዲዛይን እና በደብረዘይት ማሰልጠኛ ተቋም የመመገቢያ አዳራሽ ጥናትና ዲዛይን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 008/17


 

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት የዋና መ/ቤትና ደብረዘይት ማሰልጠኛ ተቋማቱ ላይ የሚሰሩ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት ጥናትና ዲዛይን እና በደብረዘይት ማሰልጠኛ ተቋም የመመገቢያ አዳራሽ ጥናትና ዲዛይን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚወዳደሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡ በዚህም መሰረት፡-

  1.  ለጥናትና ዲዛይን አገልግሎቶች:-

1.1 በፍሳሽ አወጋገድ ጥናትና ዲዛይን ስራ ላይ መወዳደር የፈለገ፣ በዘርፉ ለግብር ዘመኑ የታደሰ ደረጃ አንድ የአማካሪነት ፍቃድ ያለው፣ በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

1.2 በመመገቢያ አዳራሽ ጥናትና ዲዛይን ስራ ላይ መወዳደር የፈለገ፣ በዘርፉ ደረጃ ሶስትና ከዚያ በላይ ለግብር ዘመኑ የታደሰ የአማካሪነት ፍቃድ ያለው፣ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

  1.  ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 አቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።፡

  2.  የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሻል እና ቅድመ መገምገሚያዎችን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡

  3.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በየሎቱ /የጨረታ ሰነድ ላይ/ የተገለፀውን ብር በሲፒአ ወይም በባንክ ዋስትና ከቴክኒካል /ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ እሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

  4.  ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከ4፡30 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የአከፋፈት ቅደም ተከተሉም፡-

5.1. የፍሳሽ አወጋጋድ ስርዓት ጥናትና ዲዛይን ጨረታ፣

5.2. የመመገቢያ አዳራሽ ጥናትና ዲዛይን ይሆናል፡፡

  1. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

  2. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደአስፈላጊነቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598 /0118-694931 ከሳህሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ 


 

የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት


 

Save Tender