በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡-009/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
• ሎት አንድ - የሚኒባስ እና የአውቶሞቢል ኪራይ
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ፕሮፖዛል “አንድ ኦሪጅናል ኮፒ” እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦሪጅናል ኮፒ” የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ በኤንቨሎፕ በማቅረብ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን (በሚቀጥለው የስራ ቀን) ከቀኑ 4፡00 ሰዓት በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 202 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ጠቅላላ ከሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት አንድ 5,000.00 (አምስት ሺህ) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ CPO መስራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሚል አድራሻ መሆን አለበት፡፡
ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት ጨምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎት ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ /ቫት/ ጨምሮ ወይም ተ.እ.ታ /ቫት/ በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያልተገለፁ ከሆነ ተ.እ.ታ /ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀባቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ባሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሳቸውን ከጨረታው ካገለሉ እና የጨረታው አሸናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም እቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት ናሙናዎችን ለግዥ አገልግሎት ቡድን ማስገባት አለባቸው፡፡
አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር፡- 011-5-57-57-42/ 011-5-57-57-19 በመደወል ወይንም ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ህብረት ፊት ለፊት አማጋ ህንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
