በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቁሉምሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የዋና በርና የአጥር ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቁሉምሳ ግብርና ምርምር ማዕከል
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቁሉምሳ ግብርና ምርምር ማዕከል የዋና በርና የአጥር ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ፡-
-
ተጫራቶች አግባብነት ያለው የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN /፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ምዝገባ ሰርተፊኬት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
-
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ያሉ B.C ተቋራጭ የሆኑ የግንባታ ስራ ፈቃድ ያላቸውና የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
-
ለሚቀርበው አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒአ /CPO/ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ዋስትና ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ የያዘ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/ ከቁሎምሳ ግብርና ምርምር ማዕከል ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ ድረስ በአካል ቀርበው በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ::
-
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21 ቀናት ማዕከሉ ለዚህ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት በ22ኛው ቀን /የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን/ በቁሉምሳ ግብርና ማዕከል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
-
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
-
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥሮች፡ 0911545707/0936059361/0222380029 ቁሉምሳ (አሰላ) መጠቀም ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቁሉምሳ ግብርና ምርምር ማዕከል
