Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ኮንሶ ፡ ደቡብ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0945603600
  • Website
  • Deadline12 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-12 00:00:00
  • Categories

በደ/ኢ/ክ/መ/ የኮንሶ ዞን የካራት ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በካራት ከተማ አስተዳደር የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም-5 ለተለያዩ አገልግሎት የሚዉል የፋብሪካ ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ


 

በደ/ኢ/ክ/መ/ የኮንሶ ዞን የካራት ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በካራት ከተማ አስተዳደር የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም-5 ለተለያዩ አገልግሎት የሚዉል የፋብሪካ ውጤቶች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው ለመወዳደር ለምትፈልጉ ተጫራቾች/ ድርጅቶች፡-

1/ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው።

2/ በዘርፉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።

3/ በዘርፉ/TIN Number/የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ያላቸው።

4/ በዘርፉ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ያላቸው።

5/ በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው።

6/ በዘርፉ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ያላቸው መሆን አለባቸው።

7/ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዘርፍ የዕቃው ዓይነት ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለሥልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመቅረብ 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ካራት ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት/ግ/ፋ/ን/አስ/ር ዋና ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር- 6 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

8/ በዘርፍ ላይ ለመወዳደር የምትፈልጉ ዕጩ ተጫራቾች የዕቃው ዝርዝር የያዘና ቴክኒካል ሰነድ ብቻ ለብቻ በአንድ አንድ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ቴክኒካልና ፋይናንሻል እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ማለትም ቴክኒካል ኮፒ 1፣ ኮፒ-2 እና ፋይናንሻል ኮፒ-1፣ ኮፒ-2፣ ቴክኒካል ኦርጅናል 1 እና ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በቴክኒካል ኦርጅናል ውስጥ በማስገባት በትክክል በማሸግ፤ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ፣ ስም፣ ፊርማ እና አድራሻ በመግለጽ በየዘርፉ ስድስት ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9/ የጨረታው ሳጥን በ16ተኛው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

10/ ዕጩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ የተረጋገጠ ቼክ  /CPO/ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ከቴክኒካል ኦርጅናል መረጃዎች ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11/ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።

12/ አሸናፊው ድርጅት ላሸነፉበት ዕቃ የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10% ይዘዉ ቀርቦ ውል ባይገባ በዘርፉ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግሥት ውርስ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።

13/ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾ የሚሰጠው በትዕዛዝ መሠረት አቅርቦቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ለመ/ቤታችን ማስረከብ ይኖርበታል።

14/ የጨረታው ሳጥን ይከፈታል በተባለበት በ16ኛው ቀን በመንግሥት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

15/ ተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታው አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት ሊያስተጓጉል አይችልም።

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- 09-76-14-36-45፣ 09-20 98 00-30፣ 09 13-89-17-79


 

በደ/ኢ/ክ/መ/ የኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አስ/ር/ፋ/ጽ/ቤት 

ካራት


 

Save Tender