በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ከዚህ በታች የተገለፁትን የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ከዚህ በታች የተገለፁትን የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
1. ሎት 1 የደንብ ልብስ
2. ሎት 2 የተለያዩ ጫማዎች
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ህጋዊ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
-
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ግዥ አቅርቦት እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
-
ተጫራቾች በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በዘርፉ በዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
-
ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድና ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው
-
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻው 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየትና በማሸግ ሁለቱንም በአንድ ፖስታ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት አዳራሽ ይከፈታል።
-
የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ (እሁድ ወይም የሕዝብ በአላት) በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
-
የዕቃ ማስረከቢያ ቦታ የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡
-
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033-551-02-05፣ 033-551-22-68፣ 033-551-30-02
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የኮምቦልቻ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ኮምቦልቻ
