የደ/ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
Debre Berhan Health Science College (የደ/ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-05/2017
የደ/ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2017 በጀት ዓመት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
-
የፅዳት እቃ ሎት3
-
የኤሌክትሮኒክስ እቃ ሎት 10 በመሆኑም
-
በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
-
በዘርፉ አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
-
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
-
የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት /vat/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
-
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
-
በጨረታው የሚቀርበውን ዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
-
ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት 11፡30 ሰዓት ድረስ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይቻላል።
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሎት በቁጥር በሚከተለው ሰንጠረዥ በተቀመጠው የብር መጠን /በሲፒኦ/ አሰርተው ማስያዝ አለባቸው፡፡
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ መያዝ ያለበት ብር |
|
1 |
የፅዳት እቃ ሎት3 |
ብር 6000.00 /ስድስት ሺህ ብር/ |
|
2 |
የኤሌክትሮኒክስ እቃ ሎት 10 |
ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ |
-
የግዥው ከብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ኮሌጁ ቫት የሚሰበስብ መሆኑንና የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ፣ ብሄራዊ በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናስታውቃለን፤
-
ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ዶክመንት /ሰነድ/ በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡31 ላይ ጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፤ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤ መ/ቤቱ በጥቅል ወይም በነጠላ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው።
-
ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት በቢሮ ቁጥር 6 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በ3/08/2017 ዓ.ም የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
-
አሸናፊው ተጫራች እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት ኮሌጁ በሚገኝበት መጋዘን ቦታ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
-
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
-
ተጫራቾች የሚሞሉት የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከነ ቫቱ መሆን አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ከቀረ መ/ቤቱ ቫት እንደተካተተ አድርጎ ይወስዳል።
-
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 011-681-46-40 በስልክ ቁጥር 011 681-61-90 ፣ 0116811994 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የደ/ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
