በሲዳማ ክልል የሆኮ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በካፒታል ሊያሰራ ላቀደው የህዝብ አዳራሽ ግንባታ ስራ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በሲዳማ ክልል የሆኮ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ክልል የሆኮ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በካፒታል ሊያሰራ ላቀደው የህዝብ አዳራሽ ግንባታ ስራ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት
-
ደረጃቸዉ GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆነ በዘርፉ ህጋዊ የግንባታ ፍቃድ ያለዉ ሥራ ተቋራጭ 2017 ዓ.ም ፍቃደቸዉን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /VAT registration certificate / ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም ከሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ፣ ሕጋዊ ሰዉነት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡
-
በግንባታ አፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጠዉ ተቋራጭ ጨረታውን መወዳደር አይችልም።
-
አስፈላጊውን የግንባታ ማተሪያሎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበዉ ግንባታውን መስራትና ማጠናቀቅ የሚችሉ።
-
የስራ ተቋራጮች ለመወዳደር ያቀረቡትን ብቃት/ቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና አርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር የሚችሉ ይህ ተጣርቶ ኮፒ እና ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛው ካልሆነ ተቋራጭ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል።
-
የጨረታ ማስከበሪያ /bid security/ ብር 300,000 /ሶስት መቶ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና /CPO/ ከመጫረቻ ቴክኒካል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው። ከዚህ ዉጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም ።
-
የስራ ተቋራጮች የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር /TIN NO/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ /VAT registration certificate/ ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም የጨረታ ዶክመንት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛዉ ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን በሆኮ ወረዳ ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት 500 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከሆኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መዉሰድ ይችላሉ።
-
የሥራ ተቋራጮች በተጫራቶች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፍቃዳቸዉንና ተ.እ.ታ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ የማይመለስ 500 ብር በመክፈል በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን የሆኮ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል የከፈሉበት መረጃ በመያዝ የሆኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ።
-
የስራ ተቋራጮች ጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ቦታ /site visit/ በራሳቸዉ ወጭ አይቶ ማረጋገጥ አለባቸዉ። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከሆኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። (Arithmetic error) 2% በላይ መሆን የለበትም ። ከላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታዉን መከፈት አያስተጓጉለዉም ::
-
የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረዉም ::
-
ጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተገለጸዉ ቦታና ሰዓት ይሆናል ።
-
አሸናፊዉ ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድሚያ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል።
-
አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
-
በሲዳማ ክልል ውስጥ 3 እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶችን ውል ገብቶ ግንባታ እያከናወኑ ያሉና ያላስረከቡ ስራ ተቋራጮች ይሄንን የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም።
ለበለጠ መረጃ 0916525511/0912134674
የሆኮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
